Smart UI Panel
የስርዓት ፈጣን እይታ

የቀን መረጃ እና ዋና አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ ይከታተሉ።

24/7 ተደራሽነት
100% ዲጂታል ወረቀት-ነጻ
Fast ፈጣን ፍለጋ እና ክትትል
Secure የተጠበቀ መረጃ

ደብዳቤ አስተዳደር

መሰረታዊ አላማ (Objectives)

  • አስፈላጊ መረጃዎችን ፈጥኖ እና በቀላሉ በማግኘት የህብረተሰቡን እርካታ ማሳደግ እና የመልካም አስተዳደር አሰራርን ማስረፅ።
  • ደብዳቤዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል በማድረስ የጊዜ እና የወረቀት ብክነትን ማስቀረት።
  • በወረቀት ላይ ያሉ ነባር መረጃዎችን ወደ ዘመናዊ ዲጂታል ዳታቤዝ በመቀየር አስተማማኝ የክምችት ማህደር መፍጠር።
  • ያረጁ እና በፋይል ሣጥን የተከማቹ አሰራሮችን በማስቀረት እጅግ ዘመናዊ፣ ምቹና ተደራሽ የሥራ አካባቢን መገንባት።
  • የደብዳቤዎችንና ፋይሎችን የጉዞ ሂደት በትክክል በመከታተል ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር መዘርጋት።
  • የተቋሙን የመረጃ ደህንነት በተራቀቀ ቴክኖሎጂ እና ቁጥጥር ስር ማዋል እና ማስጠበቅ።
Office Team Collaboration Secure Digital Archive

አገልግሎቶች

የመረጃ ሀብት አስተዳደርን ማዘመን ለተቋማት ስኬት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። መረጃዎችን በተፈለገው ጊዜ እና ቦታ በማግኘት፣ ወጪን በመቀነስ፣ እና አገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ ዘመናዊ አሰራርን የሚያስፋፋ ቴክኖሎጂያዊ መፍትሄ እናቀርባለን።

ጊዜ መቆጠብ

መረጃን በቀላሉ እና በፍጥነት ፈልጎ በማግኘት ተገልጋዩን ያለምንም መጉላላት በሰከንዶች ውስጥ ለማስተናገድ የሚያስችል ዘመናዊ አሰራር።

ፋይል መላክ

ደብዳቤዎችን እና ዶክመንቶችን በአንድ ጠቅታ ለበርካታ ተቋማትና ግለሰቦች በፍጥነት ለማድረስ የምንጠቀምበት መድረክ።

ፋይል መቀበል

ከውስጥም ሆነ ከውጭ የተመሩ ሰነዶችን በተደራጀ መልኩ በመቀበል ለሚመለከተው አካል በቀላሉ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለማስተላለፍ።

ተጠያቂነትና ግልፅነት

የእያንዳንዱን ደብዳቤና ፋይል የጉዞ መከታተያ (Tracking) በማየት፣ ምላሽ የሰጡንና ያዘገዩን አካላት በቀጥታ ለይቶ ለማወቅ።

የመረጃ ደህንነት

እያንዳንዱ መረጃ በከፍተኛ ምስጢራዊነት እንዲቀመጥና ለተፈቀደላቸው አካላት ብቻ ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ አስተማማኝ ዳታቤዝ።

ወጪ መቀነስ

የወረቀት፣ የህትመት እና የማከማቻ (ቦታ) ወጪዎችን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ተቋምዎን ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል አሰራር ለማሸጋገር።

አድራሻችን

ዘመናዊ የፋይል አስተዳደር ስርዓታችንን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በማንኛውም ሰዓት ያግኙን።

Smart Letter Management System (SLMS)

ድርጅትዎን ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የወረቀት ብክነትን እና የጊዜ መጥፋትን የሚያስቀር እጅግ ዘመናዊ ሲስተም።

ቦታ

Addis Ababa, Piassa

ኢሜይል

info@fms.gov.et

ስልክ

+251-118547714

ስርዓቱን አሁን ይጠቀሙ

የደብዳቤ አስተዳደር ሂደትዎን ወደ ቀላል፣ ፈጣን እና ዘመናዊ ደረጃ ያስገቡ።